Welcome to Lideta Subcity Manager Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን ይተጋል!!

በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር
የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት

በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር
የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት

በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር
የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት

በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር
የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት

በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር
የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት

በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር
የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት

የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አስፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማደራጀት ባወጣዉ አዋጅ ቁጥር 84/2016 ዓ.ም መሰረት ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የሚሰጡ 3 ተጠሪ ተቋማት የጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት፣ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት እና የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እንዲሁም በውክልና ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተጨማሪም የወረዳ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤቶችን የመምራት፣ የመደገፍ፣ የማስተባበርና የመቆጣጠር ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡

የልደታ ክፍለ ከተማ ሥራ አስከያጅ ጽ/ቤት በስሩ የተደራጁ ተጠሪ ተቋማትን እና የወረዳ ሥራ አሰኪያጅ ጽ/ቤቶችን በማስተባበር በ2018 በጀት ዓመት ከዝግጅት እስከ ትግበራ ምዕራፍ ያሉ ቁልፍ እና አበይት ስራዎችን በተገቢው ሁኔታ በማከናወን እንዲሁም የተቋማዊ ሪፎርም ስራዎችን በልዩ ትኩረት ተግባራዊ እንዲደረጉ በመደገፍ፣ ከተቋማትና ባለድርሻ አካላትን በማቀናጅት እና በማሳተፍ የማዘጋጃ ቤታዊ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሳለጥ የማድረግ፣ የተቋማት አፈጻጸም ክትትል እና ድጋፍ የማድረግ፣ ለዘርፉና ባለድርሻ አካላት ክፍተትን መሰረት ያደረገ ስልጠና በመስጠት የመፈጸም እና ማስፈጸም አቅም የመገንባት፣ ክፍለ ከተማችን ፅዱና ውብ የስራና የመኖሪያ አካባቢ የማድረግ፣ ቀልጣፋና በቴክኖሎጂ የተጋዘ የኩነትና የነዋሪነት አገልግሎት እንዲሰጥ የማድረግ እና የእሳትና ሌሎች የአደጋዎች እንዳይከሰቱ ቅድሚያ የመከላከል እንዲሁም ... ተጨማሪ ያንብቡ

አቶ ያየህ አለም , የልደታ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ
image description

የጽ/ቤቱ ቡድን መሪና ባለሙያዎች

የልደታ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አስተዳደር ጽ/ቤት ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የለውጥ ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በብቃቱና እና በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ የሰው ኃይል እንዲመራ በማድረግ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡

በተጨማሪም በጽ/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሠራተኞች በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት ፍህታዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና ተገልጋዮች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው ግንዛቤ በመፍጠር በዚህም ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር፣ በህዝብና መንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር፣ ልማትና ዲሞክራሲ እንዲያብብ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በመሆኑም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂት ለመፍታት በምናደርገው ጥረት ባለድርሻ አካላትና ህብረተሱቡ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ጎን እንዲቆሙ እናሳስባለን፡፡