Welcome to Lideta Subcity Manager Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የብልጽግና ተምሳሌት ሆና ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

ቆሻሻን በተገቢው መንገድ በማስወገድ ምቹ የመኖሪያ አካባቢ እንዲፈጠር እየሰራ መሆኑን የልደታ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ገለጸ።

ጥቅምት 24, 2018
ጽ/ቤቱ ከተማ አቀፍ በማሆበረሰቡ የደረቅ ቆሻሻ ከምንጩ የመለየት ንቅናቄ ማስጀመሪያ ፕሮግራም አካሄደ። በፕሮግራሙ ላይ የጽዳት አምባሳደሮች፣ባለሙያዎች፣የሽርክና ማህበራት፣ ነዋሪዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል። በፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የልደታ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ያየ ዓለም እንደገለጹት የደረቅ ቆሻሻ አያያዝን በማስተካከልና ከምንጩ በመለየት በቅብብሎሽ በማጓጓዝ የሚፈለገው ቦታ በማድረስ አካባቢያችንን በንጽህና በመያዝ ለመኖሪያ ምቹ እንድትሆን በመተባበር ልንሰራ የሚገባ መሆኑን ገልጸዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት አዲስ አበባ ከተማን ገጽታ የቀየሩ በርካታ የልማት ስራዎች መሠራታቸውን ገልጸው ቆሻሻን በየቦታው ከመጣል ተቆጥበን ቆሻሻን በአግባቡ በመለየትና መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል አካባቢያችን ለመኖሪያ ምቹ የተጀመሩ የልማት ስራዎችም ቀጣይ እንዲሆኑ መስራት የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን ተናግረዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች