Welcome to Lideta Subcity Manager Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የብልጽግና ተምሳሌት ሆና ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

የመሠረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ፈጣን፣ ቀልጣፋና ግልፀኝነት የተላበሱ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸው ተገለፀ።

ታህሳስ 21, 2018
በልደታ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት እና ተጠሪ ተቋማት እየተሰጡ ያሉ አገልግሎቶች ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ግልፀኝነት የተላበሱ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ገለፀ። ከአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት እና ተጠሪ ተቋማት የተውጣጣ የምልከታ ቡድን በልደታ ክ/ከተማ ለተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የነበረው የመሠረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የስራ እንቅስቃሴ በመስክ ምልከታ ያሉበት ደረጃ ተወዋውሮ የተመለከተ ሲሆን የግኝቱ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። የምልከታ ቡድኑን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ አማካሪ አቶ ይብሬ ኢስማኤል ሲሆኑ ባካሄድነው የመስክ ምልከታ በተቋማቱ የነዋሪውን የመልካም አስተዳደር ችግር ፈቺ የሆኑ ተግባራት መከናወኑን ተገንዝበናል ብለዋል። አቶ ይብሬ አክለዉም በተቋማቱ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱ በቴክኖሎጅ መዘመኑ፣ ሥራዎችን ከሌሎች ተቋማት ጋር ተናባቢ በሆነ መልኩና ቅንጅታዊ አሠራርን ባጠናከረ መልኩ በመፈጸሙ እምርታዊ ለዉጥ ማምጣት የተቻለበት ስራ መሠራቱን ገልፀዋል። በክ/ከተማው የሚገኙ የመሠረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፈጣን፣ ቀልጣፋና ስሉጥ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት በማረጋገጥ ረገድ የመጣዉን ለዉጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አቶ ይብሬ አሳስበዋል። በዚሁ መድረክ ላይ በሁሉም ተጠሪ ተቋማቶች ሰፋፊ ስራዎች የተከናወኑበት መሆኑ የተገልፀ ሲሆን በተለይም ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ከህብረተሰቡ የሚነሱ ቅሬታዎችን መፍታት የቻልንበት፣ የሚሰጡ አገልግሎቶች በይበልጥ ከቴክኖሎጂ ጋር ተሳስረው ማዘመን የቻልንበትና በዚህም እምርታዊ ለውጥ የመጣበት መሆኑ ተመላክቷል። የክ/ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤቱ እና ተጠሪ በሆኑት የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት፣ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ቅርንጫፍ፣ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር፣ በፅዳት አስተዳደርና በአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አገልግሎት አሰጣጥና ሌሎች የስራ እንቅስቃሴዎች ላይ ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ ምልከታ መደረጉ ከመድረኩ መረዳት ተችሏል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች