Welcome to Lideta Subcity Manager Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የብልጽግና ተምሳሌት ሆና ለማየት ይተጋል!!
image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ የ2 ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች የጂ+4 ማስፋፊያ ግንባታ ማስጀመሪያ ተካሄደ

ታህሳስ 22, 2018
በክ/ከተማው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የፍሬህይወት ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች የጂ+4 የማስፋፊያ ግንባታ ማስጀመሪያ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በማስፋፊያ ግንባታው ማስጀመሪያ ወቅት እንደተናገሩት ከተማችን አዲስ አበባን ህፃናትን ለማሳደግ ምቹ ከተማ እናደርጋለን የሚለውን የክብርቲ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ኢንሼቲቭ ወስደን በትምህርቱ ዘርፍ በመተግበር እና ትውልድ ግንባታ ላይ ትኩረት አድርገን በመስራት አበረታች ውጤት አስመዝግበናል ሲሉ ገልፀዋል። የማስፋፊያ ግንባታው የትምህርት ተደራሽነትን፣ ጥራትን እና ደረጃን በማሻሻል የመማር ማስተማር ስራን ለማሳለጥ እየሰራነው ላለው ተግባር አጋዥ ይሆናል ያሉ ዶ/ር ዘላለም ግንባታው በአጠረ ጊዜ ተጠናቆ ወደ ተግባር እንዲገባም በቅንጅት ይሰራል ትምህርት ቢሮም ክትትል ያደርጋል በማለት ገልፀዋል። ለትውልድና ለሀገር ግንባታ ቅድሚያ ሰጥቶ ይህንን የማስፋፊያ ግንባታ ወደ ተግባር ላስገባ የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደርም በት/ቢሮ ስም እናመሰግናለን በማለት ገልፀዋል ዶ/ር ዘላለም። የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደተናገሩት ዛሬ ያስጀመርነው የማስፋፊያ ግንባታ በመምህራን፣ በወላጆችና በተማሪዎች ዘንድ ለረጅም ዓመታት የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖ ሲነሳ የነበረ ነው ብለው አስተዳደሩም ይህንን የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ ግንባታውን አስጀምሯል ሲሉ ገልፀዋል። የማስፋፊያ ግንባታው የትምህርት ስርዓቱን ለማሻሻል እየተሰሩ ላሉ ተግባራት ተደማሪ አቅም ይሆናል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተቋማትን በአሰራር እና በአደረጃጀት እንዲዘምኑ በማድረግ በእውቀትና በስነ-ምግባር የታነፀ ትውልድን ለመፍጠር በትጋት እንሰራለን በማለት ገልፀዋል። ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አክለውም መንግስት ከለውጡ በፊት በትምህርት ዘርፉ በየነበሩ ስብራቶችን በመጠገን በእውቀት የዳበረ ተመራማሪ የሆነ ሀገርን የሚረከብ ትውልድ ለመገንባት እየሰራ ነው ብለው እንደ ልደታም ተግባሩን ስኬታማ ለማድረግ በትኩረት እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች